መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በስቶኮልም የሚገኝ አንድ ሬስቶራንት የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ-ጂፒንግ ምስል በቢጫ የሌሊት ወፍ ጆሮ በማድረግ በመለጠፉ ዘረኛ ድርጊት ነው በሚል እየተተቸ ይገኛል፡፡ ከኮሮና ቫይረስ መነሻ ጋር በማያያዝ በእስያውያኑ ላይ የሚደርስ የዘር መድሎ እየተበራከተ ይገኛል፡፡

~ በቤላሩስ በፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፤ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ዜጎችን ፖሊስ በውሃ አማካይነት መበተኑ ተሰምቷል፡፡

~ ፍልስጤማዊው ታራሚ በእስራኤል ማረሚያ ቤት ውስጥ ለ 77 ተከታታይ ቀናት የምግብ አድማ ስጋት ወልዷል፡፡ ማህር አል አክሃራስ በቁጥጥር ስር የዋልኩበት መንገድ ፍትሃዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ምግብ ያለመብላት አድማ እያደረገ ይገኛል፡፡

~ የ.ተ.መ.ድ የሊቢያ ልዑክ በቀጣይ ወር በሀገሪቱ የሚገኙ ሃይሎች የፊት ለፊት ድርድር ያደርጋሉ ሲል አስታወቀ፡፡ የሊቢያ ብሄራዊ የነዳጅ ኮፖሬሽን አቋርጦት የነበረው የሻራራ የነዳጅ ምርት ስራን በትላንትናው እለት ጀምሯል፡፡ የሻራራ የነዳጅ ማጣሪያ በሀገሪቱ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ስፍራ ነው፡፡

~ በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 150ሺ መብለጡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

~ በብራዚል ዋንኛ የውንጀላ ቡድን መሪ የሆነው አንድሬ ኦሊቬራ ማሲቶ ከእስር መለቀቁ ተቃውሞ አስነሳ፡፡

~ በሳዑዲ አረብያ የዲሞክራሲ ትግል አንቂና መንግስት በሰብዓዊ መብት ረገጣ ዙሪያ በመተቸት የሚታወቀው ሼኮ ሞሃመድ ቢን ዳሊማ አል ቋሃታኒ በስትሮክ እየተሰቃየ መሆኑ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ በማረሚያ ቤት ውስጥ ሆኖ በመንግስት ሆን ተብሎ ተመርዟል በሚል ይነገራል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *