መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2013-በሊቢያ አይኤስ በግፍ ከገደላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል በህይወት ተርፌ መጣው ያለው ግለሰብ በሌላ ወንጀል በእስር ተቀጣ፡፡

በባሌ ዞነ ጎባ ወረዳ ኢፍቱ ሹራ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆነው ወጣት ሱልጣን የኑስ በዛው ቀበሌ ውስጥ ልዩ ቦታው ጎሮ በተባው ስፍራ ጥር 30 ቀን 2012ዓ.ም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የአስራ ሶስት ዓመት ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ክሱን ሲከታተል የቆየው የጎባ ዞን ፍርድ ቤት ተጠርጣሪው ጥፋተኛ በማለት ጥቅምት 03 ቀን 2013ዓ.ም በዋለው ችሎት በስድስት ዓመት ከስምንት ወር እስራት እንዲቀጣ ብይን ተሰቶበታል ሲሉ በኦሮሚያ ፖሊስ የባሌ ዞን ሚዲያ እና ኮምንኬሽን ባለሙያ ናስር ኡመር ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *