መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2013-በምስራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ሦስት ወራት በትራፊክ አደጋ የ57 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል


በምስራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት 3 ወራት ውስጥ በደረሰው 74 የትራፊክ አደጋ የ 57 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተነገረ ሲሆን የትራፊክ አደጋው ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2.6 በመቶ መቀንሱ ተገልፆል፡፡
ከሟቾች በተጨማሪ በ29 ሰዎች ላይ ከባድ በ45 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሩብ አመቱ ምንም አይነት የትራፊክ አደጋ ያልተከሰተባቸው ወረዳዎች ሰዴ፣ቢቡኝ፣ እነብሴ ሳር ምድር እና ባሶሊበን ወረዳዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ደንብ በመተላለፋቸው 10ሺ 461 አሽከርካሪዎች፣ረዳቶች፣ ባለሃብቶችና እግረኞች ተከሰው በጥፋታቸው በመቀጣታቸው 4 ሚሊየን 771 ሺ ብር ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

ለትራፊክ አደጋ መከሰት የተለያ ምክንያቶች ቢኖሩም ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው ከመጠን ያለፈ ፍጥነት በመሆኑ የክልሉ መንግስት በከፍተኛ ወጭ በገዛቸው ራዳሮች የቁጥጥር ስራን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *