መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2013-የዲሞክራቶች የፕሬዝዳንታዊ እጩ ጆ ባይደን በፍሎሪዳ ትራምፕ የነበራቸው የምረጡኝ ቅስቀሳ ዜጎችን ለኮሮና ቫይረስ አጋላጭ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በደቡባዊ ፍሎሪዳ ባይደን በትላንትናው እለት በነበራቸው ስብስብ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳለፍነው ሰኞ ያደረጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያደረጉ ጥቂቶች ናቸው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ትራምፕ በትላንትናው እለት በፔንስላቪያ ግዛት በነበራቸው የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን መጥፎ ሰው ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸው በቀጣይነት በሰሜናዊ ካሮላይና እና ጆርጂያ የሚያደርጉ ሲሆን በድጋሚ በፍሎሪዳ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ያደርጋሉ፡፡

የፍሎሪዳ ግዛት በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ከሚያስገኙ ግዛቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በምርጫው ባይደን ሊያሸንፉ እንደሚችል ከህዝብ የተሰበሰበ ድምፅ ይጠቁሟል፡፡ በመካከላቸው የ 10 ነጥብ ልዩነት አሉ፡፡

በፍሎሪዳ ግን የጆ ባይደን የማሸነፍ ግጭት ከትራምፕ በ 3.5 በመቶ ብቻ የበለጠ ነው፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *