መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 5፤2013-በሞዛምቢክ በውሃ ሙላት ሳቢያ ማዕድን ቁፋሮ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 16 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ

በሰሜናዊ ሞዛምቢክ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋው የደረሰ ሲሆን ፤ በማዕድን ቁፋሮ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 16 ሰዎች ሕይወታቸውን ማለፉን የሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል፡፡ አሁንም ቀሪ ሰራተኞች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰው ሊያሻቅብ ይችላል፡፡

አደጋው የደረሰበት ናምፑላ አውራጃ አስተዳዳሪ ፋሩክ ሳታር ፤ መጀመሪያውኑ ስራውን በሚከውኑበት ስፍራ የተጠራቀመ ውሃ መኖሩ አደጋውን ስለማባባሱ ጠቅሰዋል፡፡

በማኒካ አውራጃ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በአደጋው ህይወታቸው ማለፉን ሀገሪቱ ሪፖርት አድርጋለች፡፡

የሞዛምቢክ ብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ተቋሙ ይፋ እንዳደረገው ፤ 1,194 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንና የምግብ እንዲሁም ሌሎች አቅርቦቶች እንደሚሹ ገልጿል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *