መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 5፤2013-በባህርዳር ከተማ መሳሪያ የታጠቁ ዘራፊዎች አባይ ማዶ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ማደያ የስርቆት ወንጀል ፈፀሙ፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው በባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ማደያ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በቪትዝ መኪና በመሆን ከቀኑ 5፡00 ላይ ገንዘብ ያዥዋን በመሳሪያ በማስፈራራት 44 ሺ ብር ይዘው ተሰውረዋል፡፡

ይህን ወንጀል የሰማው የከተማዋ ፖሊስ ወንጀሉን የፈፀሙትን ግለሰቦች ለመያዝ ባደረገዉ ጥረት አንድ ተጠርጣሪ ከነ ቪትዝ መኪናው በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ምርመራውም በባህርዳር ከተማ በሚገኘው 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ እየተጣራ የሚገኝ መሆኑን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የሰላምና የደህንነት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *