መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 5፤2013-በኢትዮጲያ ከሁለት ሚሊየን በላይ ኮንዶም በጥራት ችግር የተነሳ ከአገልግሎት ውጪ በመሆኑ የኮንዶም እጥረት አጋጥሟል

በኤች አይ ቪ መከላከል እና መቆጣጠር ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጽጌሬዳ ክፍሌ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩ የኮንዶም ግዢ በመንግስት በኩል ሲፈጸም ዋጋ ላይ በማተኮር ለጥራት የሚሰጠው ቦታ ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ገልፀዋል።

የኮንዶም ግዢ ሲፈጽም የጥራት መለኪያ ተብሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸው ተረጋገጠ መሆኑን በመመዘን ተገዝቶ ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኃላ በሀገር ውስጥ ላብራቶሪ ይፈተሻል።

ሆኖም ግን ባሳለፍነው 2012 አመት ከህንድ ሀገር የተገዛው ኮንዶም በተደረገበት የሀገር ውስጥ የላብራቶሪ ምርመራ የጥራት ጉድለት እንዳለበት ለማረጋገጥ ተችሏል።

የጥራት ጉድለቱ ታውቆ ሽያጩን ለፈጸመው የህንድ ኩባንያ የሸጠወን ኮንዶም እንዲመልስ ጥያቄ ቢቀርብም መመለስ አለመቻሉ ችግሩን አባብሶታል።

ይህ በመሆኑ መከፋፋፈል የነበረበት ከሁለት ሚሊየን በላይ ኮንዶም ተቀማጭ እንዲሆን በመደረጉ የኮንዶም እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ስለመሆኑ ዶ/ር ጽጌሬዳ ክፍሌ ለብስራት ሬድዮ ጨምረው ተናግረዋል።

መንግስት በየዓመቱ ከ2 ሚሊየን በላይ የኮንዶም ግዢን የሚፈጽም ሲሆን ችግሩን ለመፍታት እንዲቻል ድንገተኛ ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ የሚሰጥ ግብረሃይል ተቋቁሟል።

ሪፖርተራችን ቤተልሄም እሸቱ ከአዳማ በላከችው ዘገባ በኢትዮጲያ በኮንዶም ጥራት ችግር የተነሳ የኤች አይ ቪ ስርጭት መጨመሩን ያመላክታል።

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *