መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 5፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች

~ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወንድ ልጅ ባሮን በኮሮና ቫይረስ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ምልክቱን ሳያሳይ ነጻ መሆኑን ወላጅ እናቱ ሚላኒ ትራምፕ ተናገሩ፡፡

~ ደቡብ ሱዳን የገንዘብ ኖት ለዉጥ ልታደርግ ነዉ መባሉን አስተባበለች፡፡ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በመረጃ ሚንስትሩ በኩል ደቡብ ሱዳን የገንዘብ ለዉጥ ልታደር ነዉ በሚል የተሰራጨዉ መረጃ የሀሰት ነዉ በኢኮኖሚስቶች ተጠንቶ ከቀረበ ምክክር ዉጪ እቅድ የለም ብለዋል፡፡

~ ቱርክ አዘርባጃንና አርሜንያ ግጭት ወደ ገቡበት የናጎርኖ ካራባክ ግዛት የሶርያ ታጣቂዎችን አስገብታለች መባሉን አስተባበለች፡፡

~ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ አካባቢ የሶማሊያ ወታደሮች ከአልሻባብ ታጣቂዎች ጋር በገቡበት የተኩስ ልዉዉጥ ቢያንስ 13 ወታደሮቭ መገደላቸዉ ተሰማ፡፡

~ በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እና በሌሎች ስምንት ከተሞች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት የተነሳ በምሽት እንቅስቃሴን የሚከለክል ህግ መተላለፉን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኔኤል ማክሮን አስታወቁ፡፡

~ የአለም የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መዛመቱ መቀጠሉን ተከትሎ በቲቢ ህይወታቸዉን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በቀጣይ አመታት ሊጨምር እንደሚችል ያሰጋኛል ሲል አስታወቀ፡፡
~ በየመን የእስረኞች ልዉዉጥ በኢራን በሚደገፉ የሃዉቲ ሀይሎች እጅ ስር የነበሩ ሁለት አሜሪካዉያን ከእስር ሲለቀቁ፤በምላሹ 240 የሀዉቲ ታጣቂዎች ከእስር ተለቀዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *