መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፣2013-በናጎርኖ ካራባክ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የመድረስ ተስፋ እየጨነገፈ መምጣቱ ተሰማ

አዘርባጃንና አርሜንያ የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው በመቀጠላቸው የተነሳ በተራራማው ክፍል በሚወዛገቡበት ስፍራ የተኩስ አቁም ለመድረስ አዳጋች እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አሊየቪ እንዳስታወቁት የሀገሪቱ ጦር ግዛቶቹን የማስመለስ ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፤ይህም የአርሜንያ አሉታዊ እርምጃ የሚቀጥለዉ ከሆነ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አርሜንያ በበኩሏ በአካባቢዉ የረድኤት ድጋፍ የጫኑ አዉሮፕላኖች እንዳይንቀሳቀሱ የአዘርባጃን ደጋፊ የሆነችው ቱርክ ጫና እየፈጠረች ነዉ ስትል ከሳለች፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለአዘርባጃን በወሰነላት ስፍራ የአርሜንያ ጎሳዎች የሚኖሩ ሲሆን ባሳለፍነዉ ቅዳሜ የተደረሰበት የተኩስ አቁም ስምምነት 24 ሰዓት እንኳን ሳይዘልቅ ሀገራቱን ወደ ተኩስ ልዉዉጥ አስገብቷል፡፡

የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አሊየቪ የሰላም ድርድሩ መጀመር የሚችለዉ ቱርክ፣አሜሪካና ሩሲያ ባሉበት የአደራዳሪዎች ቡድን ቱርክ ስትካተት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ለስምምነቱ አርሜንያ የያዘችዉን ስፍራ ትልቀቅ ስትል አዘርባጃን ተናግራለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *