መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፣2013-በኢትዮጲያ ከሚመዘገበው የካንሰር ተጠቂዎች 32 በመቶ ድርሻ ያለው የጡት ካንሰር ነው ተባለ።

የጡት ካንሰር ሴቶችን በከፍተኛ መጠን ለሞት ከሚያደርጉት የካንሰር ዓይነቶች ዋንኛው ሲሆን በኢትዮጲያ ከሚመዘገበው የካንሰር ተጠቂዎች ውስጥ 32 በመቶ ድርሻ እንዳለው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካንሰር ህክምና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ታከለች ሞገስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የጡት ካንሰር ከተጠቂወች አንጻር ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዝ እና በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጠዉ ደግሞ በሴቶች ላይ የሚከሰተው የማህጸን በር ካንሰር መሆኑን አንስተዋል፡፡

የካንሰር ህመሞች መነሻ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም በቤተሰብ የነበረ የጡት ህመም ወይም ካንሰር ፤ከፍተኛ ውፍረት ፤ ዘግይቶ ልጅ መውለድ፤ የአልኮሆል እና ሲጋራ ተጠቃሚነት፣ የሆርሞን ህክምና ፤ለጨረር መጋለጥ፤የወር አበባን በለጋ ዕድሜ መጀመር፤የወር አበባን ለረጀም ጊዜ ወይም ዕድሜ ማየት ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ምክንያቶችን መሆናቸውን ባለሙያዋ ገልጸዋል።

የጡት ካንሰር እንደተከሰተ ወዲያው ወደ ሰውነት ሳይሰራጭ በወቅቱ ህክምና ማግኘት ከተቻለ 90 በመቶ የሚሆነው የጤና እክል ማስቀረት ይቻላል፡፡

በኢትዮጲያ በሚገኙ 12 ሆስፒታሎች ውስጥ የጡት ካንሰር ህክምና ይሰጣል፡፡ዓለም አቀፉ የጡት ጤና ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *