መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፣2013-የብስራት የምሳ ሰዓት አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የይርግዚስታን ጠቅላይ ሚንስትር በፍቃዳቸዉ ከስልጣናቸዉ መልቀቃቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የተጣለዉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያበቃ በዛሬዉ እለት ወሰነ፡፡

~ በፈረንሳይ በትላንትናዉ እለት ብቻ 30,621 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደረገ፡፡በፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በድጋሚ ማገርሸቱን ተከትሎ በምሽት እንቅስቃሴን የሚከለክል መመሪያ ይፋ ተደርጓል፡፡

~ በሆንግ ኮንግ በፖለቲካ ወንጀል ለሚፈለጉ ሰዎች ካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ከመስጠት ተግባሯ ታቁም ስትል ቻይና አስጠነቀቀች፡፡በቻይና ለሆንግ ኮንግ የተዘጋጀዉ የብሄራዊ ደህንነት ህግ የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎችን በማስቆጣት ለከፍተኛ ተቃውሞ መዳረጉ ይታወቃል፡፡

~ በፓኪስታን ባሎቺስታን ግዛት በሁለት አካባቢዎች የተጠመደ ቦምብ በትላንትናዉ እለት ፈንድቶ 12 ሰዎች መገደላቸዉ ተሰማ፡፡ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን ወሰደ አካል የለም፡፡

~ የአለም የጤና ድርጅት ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን እየተሰጡ በሚገኙ መድሃኒቶች ላይ በሰራዉ ምርመራ የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቀተኛ ነዉ ሲል አስታወቀ፡፡ምርመራ የተደረገባቸዉ አራት መድሃኒቶች ሲሆኑ ረድምሲቭር፣ሃይድሮክሲክሎሮኪን፣ሎፒናቪር እና ኢንተርፌሮን ናቸዉ፡፡

~ ለተቃዉሞ በወጡ የናይጄሪያ ዜጎች ላይ የሀይል እርምጃ የወሰደው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡በናይጄሪያ የልዩ ሀይል ፖሊስ አባላት በሚወስዱት እርምጃ ዜጎች ቁጣቸዉን እየገለጹ ይገኛል፡፡

~ በአፍሪካ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ በኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተነገረ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *