መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 6፣2013-የዩጋንዳ የፍትህ ቢሮ ዋና ሀላፊ የፕሬዝዳንት እጩ የእድሜ ጣሪያ እንዲነሳ ማድረጋቸው እንደሚጸጽታቸው ተናገሩ

የዩጋንዳ የፍትህ ቢሮ ዋና ሀላፊ የሆኑት አልፎንሴ ኦዊኒ-ዶሎ ከሀገሪቱ ህገ መንግስት ላይ የፕሬዝዳንት ተወዳዳሪ እጩ የእድሜ ገደብን የሚከለክለው አንቀጽ እንዲሻሻል ማድረጋቸውን ትንሽም ቢሆን ይጸጽተኛል ሲሉ ለዴሊህ ሞኒተር ጋዜጣ ተናገሩ፡፡

የእድሜ ጣሪያው መናሳቱ በዚህ ሀገር የሰራነው ስህተት ነዉ ሁላችንም አጥፍተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዩጋንዳ ህግ እድሜው ከ75 ዓመት በላይ የሆነ ሰው ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይወዳደር የቀደመው ህግ የሚከለክል ቢሆንም ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡

በዚህ የተነሳ ሀገሪቱን ለረጅም አመታት የመሩት ፕሬዝዳንት ይዌሪ ሙሴቬኒ በ76ኛ ዓመታቸው ላይ ሆነው በድጋሚ በምርጫው የሚሳተፉበትን እድል አግኝተዋል፡፡

የዩጋንዳ ህገመንግስት ውስጥ የፕሬዝዳንቱን የእድሜ ገደብ የማንሳት ሂደትን ያለ ህዝብ ውሳኔ መከወን እንደሚቻል ይፈቅዳል፡፡ለዚህ ስህተት ሀላፊነቱን እወስዳለሁ ፍትሃዊ አልነበረም ሲሉ አልፎንሴ ኦዊኒ-ዶሎ ተናግረዋል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *