መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 9፣2013-በኢትዮጵያ በአንድ ወንጀለኛ ላይ የተላለፈ የሞት ቅጣት ውሳኔ በሁለት ዓመት ውስጥ ተፈፃሚ ካልተደረገ በእድሜ ልክ ሊቀየር እንደሚችል ተነገረ

በአለም አቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ ከሆኑ ህጎች መካከል አንዱ ሆኖ የሚቀመጠው የሞት ቅጣት ሲሆን ህጉን ተግባራዊ ካደረኩ 53 የአለም ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጲያ ናት ፡፡

ኢትዮጲያ ህጉን ተቀብላ ብታፀድቅም ተግባራዊነቱ ላይ ክፍተቶች እንዳሉ ብስራት ያነጋገራቸው ጠበቃና የህግ አማካሪው አቶ ወንድወሰን አሰግደው ተናግረዋል፡፡

ከእዚህ ቀደም የሞት ቅጣት ቢፈረድም ተግባራዊነቱ ላይ ከፍተኛ ክፍተት አለ ያሉት ሌላኛው ጠበቃና የህግ አማካሪው አቶ አበበ ዘነበ ሲሆኑ በቅርቡ የቀድሞ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማሻሻያ ሊደረግባቸው እንደሆነ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

ማሻሻያ ሊደረግባቸው ከታሰቡ ህጎች መካከል የሞት ቅጣትን የተመለከተው እንዳለበተረ ባለሙያው የገሩን ሲሆን ፤አንድ ጥፋተኛ የተፈረደበት የሞት ፍርድ በሁለቱ ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ካልተደረገ ወንጀለኛው የሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ ይቀየራል ይገኝበታል፡፡

በአውሮፓውያኑ የጊዜ ቀመር በ2020 የወጣው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ባደረጉ በ53ቱ ሀገራት በሚገኙ 620 ዜጎች ላይ የተበየነባቸው የሞት ፍርድ ተግባራዊ በመደረጉ በሞት ተቀጥተዋል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *