መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 9፣2013-በኦሮሚያ ክልል በመስከረም ወር በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ፤ የ34 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከአስራ አንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል

ባሳለፍነው መስከረም ወር ባጋጠሙ የትራፊክ አደጋዎች የ 34 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ 30 ሠዎች ላይ ከባድ ፣በ 18 ሠዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 38 የንብረት ውድመት አጋጥሟል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲተመን አስራ አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሺ ብር አንደሚገመት ተጠቁሟል፡፡

አደጋዎቹ ቡራዩ ከተማ ወረዳ 02 ፣ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ ቀበሌ 02 ፣ወልመራ እና ሰበታ ዋስ ወረዳዎች እንዲሁም ምዕራብ ሸዋ ኤሉ፣ሰሜን ሸዋ ደገም እና ግራር ጃሶ፣እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሶዶ ዳዲ ወረዳዎች ደርሰዋል፡፡

በተጨማሪም በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በራክ ፣ በምዕራብ ባሌ ዞን ቡልቅ ወረዳዎች እና በምስራቅ ሸዋ አዳሚ ቱሉ ወረዳ ቡልቡላ ከተማ ፣ቄለም ወለጋ አዋ ገላን ፣ ቡኖ በደሌ ደዴታ፣ምስረቅ ሸዋ አባ ጎቴ እና አደአ ፣በምእራብ ወለጋ ጊንቢ ፣በምስራቅ ሀረርጌ ጎሮ ጊቱ እንዲሁም በምእራብ ጉጂ ዱግዳ ወረዳዎች የደረሱ ናቸው

ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት ፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር እና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር አደጋው እንዲባባስ ምክንያት ስለመሆናቸው የኦሮሚያ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *