መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 9፣2013-በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፏኛ የተጎዳው የቻይና ኢኮኖሚ አሁን ላይ በመነቃቃት ላይ እንደሆነ ተነገረ

የአለማችን ሁለተኛዋ የግዙፉ ኢኮኖሚ ባለቤት በሆነችው ቻይና በ 2020 ዓመት ሶስተኛ ሩብ ዓመት የ 4.9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች፡፡

አስቀድሞ በሩብ ዓመቱ የቻይና ኢኮኖሚ 5.2 በመቶ ያድጋል በሚል በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ከተገመተው ያነሰ ሆኗል፡፡

በብሄራዊ ምርት እድገት (GDP) ረገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ካስከተለው ጫና የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት በማገገም ቀዳሚ ሆኗል፡፡

ቻይና በ2020 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የ 6.8 በመቶ የኢኮኖሚ መዳከም ያጋጠማት ሲሆን የተለያዩ ፋብሪካዎች እንዲሁም የማኑፋክቸር ተቋማት በቫይረሱ ምክንያት ከስራ ውጪ በመሆናቸው የተነሳ ነው፡፡

ቻይና እንዲህ አይነቱ የኢኮኖሚ ውድቀት ያጋጠማት እ.ኤ.አ ከ 1992 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *