መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 9፣2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ክፍል 1

~ አዘርባጃን ንብረትነቱ የአርሜንያ የሆነ SU-25 ተዋጋ ጄት በድጋሚ መጣሏን አስታወቀች፡፡ አዘርባጃንና አርሜንያ በናጎርኖ ካራባክ ግዛት የገቡበት ግጭት ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ከአራት ደቂቃ በኋላ በድጋሚ መጣሳቸው ተሰምቷል፡፡ 710 ያህል የጦር ሃይል አካላት ተገድለዋል፡፡

~ 5.5 ሚሊዮን መራጮች የተሳተፉበት የጊኒ ምርጫ በትላንትናው እለት ተካሂዷል፡፡ በገዢው ፓርቲ ፕሬዝዳንቱ አልፋ ኮንዴ እና በተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶአሎ መካከል ከፍተኛ ፏክክር የተደረገበት ሲሆን የምርጫው ውጤት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

~ በቺሊ እኩልነት እንዲሰፍን የተደረገው ሰልፍ ወደ ግጭት መቀየሩ ተሰማ፡፡ በግጫቱ የተነሳ ሁለት ቤተክርስቲያኖች ሲቃጠሉ ፣ በርካታ ተቋማት ተዘርፈዋል፡፡ ተቃዋሚዎች ከጄነራል አጉስቶ ፒኖቼት በኋላ ህገ-መንግስቱ መሻሻል አልቻለም ሲሉ ተችተዋል፡፡

~ በትላንትናው እለት በቦሊቪያ የተደረገው ምርጫ ውጤት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ግራ ዘመሙ የቀድሞ ፕሬዝዳንቷ ኢቫ ሞራሌስ የሌሉበት ምርጫ ሲሆን የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካርሎስ ሜሳ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ከተሰጣቸው የሶሻሊስት ፓርቲ እጩ ሉዊስ አርስ ተፋጠዋል፡፡

~ የፍልስጤም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ሳአብ አርካት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው በእስራኤል ሆስፒታል ህክምና እያደረጉ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ ከሶስት ዓመት በፊት የሳንባ ንቅለ ተከላ ህክምና ማድረጋቸው የተነገረ ሲሆን የጤናቸው ሁኔታ መወሳሰቡ ታውቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *