መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፣2013-ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለ ከተማ በመሆን ጸደቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከሰዓት ውሎው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ 11ኛው ክፍለ ከተማ እንዲሆን አጽድቋል።ምክር ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተወያየበት ወቅት ነው።

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን፣ አዳጊ የሆነውን የአገልግሎት ተደራሽነት እና የማስተዳደር አቅምን በማጎልበት ለከተማው ነዋሪዎች ሚዛናዊ በሆነ ርቀት እና ተደራሽ በሆነ መልኩ የአገልግሎት አቅርቦት በማመቻቸት ነዋሪው ፍትሐዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚረዳ ይሆናል።

በመድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን፣ ከዚህ ቀደም ከነበረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለ ከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል።

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን ዳግም የማቋቋሚያ አዋጁንም ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *