መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፣2013-ልዩ መረጃ ❗️

ያለፈውን ሳምንት፣የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣የመ/ቤታቸውን የ-3 ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል 👆

በዚሁ መግለጫ ላይ ታዲያ፣ባለፈው 2012 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ 7 በመቶ አድጋለች ሲሉ ሚኒስትሩ መናገራቸውን በርከት ያሉ የሀገር-ውስጥ ብዙሀን-መገናኛዎች ዘግበዋል ☝️

በሌላኛው አንፃር፣ትናንት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ ለህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የኢትዮጵን ምጣኔ-ሀብታዊ ክንውን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት፣ያለፈው በጀት ዓመት የተመዘገበው ዕድገት 6 ነጥብ 1 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል 👆

ይህንኑ ተከትሎም፣በጠ/ሚንስትሩ እና በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበውን የኢትዮጵያን ዕድገት የተመለከተው አሀዝ የ0 ነጥብ 9 በመቶ ልዩነት አሳይቷል በሚል ብዙዎች ግራ መጋባታቸዉን ገልጠዋል 👈

ብስራት ሬዲዮ ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቃቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ፣ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ኢትዮጵያ ያለፈውን ዓመት 7 በመቶ አድጋለች ብለው እንዳልተናገሩ ጠቁመዋል ☝️

ይልቁንስ፣ሚኒስትሩ ያለፈውን ሳምንት በሰጡት መግለጫቸው በኢትዮጵያ የተመዘገበው ዕድገት ከ6 እስከ 7 በመቶ እንደሚደርስ መናገራቸውን አቶ ሀጂ ለጣቢያችን በሰጡት ማብራሪያ አስታውሰዋል 👆

የኢትዮጵያ ዓመታዊ ዕድገት ይፋ መደረግ ያለበት በጠ/ሚንስትሩ እንደመሆኑ፣ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የዕድገት ህዳግ ከ6 እስከ 7 በመቶ ባለው ውስጥ የሚያርፍ ነው ብለው ከመናገራቸው በቀር፣ኢትዮጵያ በ7 በመቶ አድጋለች እንዳላሉ እና ስህተቱ ዜናዉን አዛብተዉ የሰሩ ሚዲያዎች መሆኑን አቶ ሀጂ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ☝️

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *