መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፣2013-የቀድሞ የኤርትራ ስደተኛ በኒውዝላንድ የህዝብ እንደራሴ አባል ሆኖ ተመረጠ


የቀድሞ የኤርትራ ስደተኛ የሆነዉ ኢብራሂም ኦማር የሌበር ፓርቲ ማሸነፉን ተከትሎ በህዝብ እንደራሴዉ ምክር ቤት የሌበር ፓርቲ 42ኛዉ ተደርጎ በዝርዝሩ ላይ ስሙ ሰፍሯል፡፡
የጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደርን ፓርቲ ማሸነፉን ተከትሎ ኢብራሂም በምክር ቤቱ መቀመጫን ያገኛል፡፡በኒውዝላንድ ህግ የምክር ቤት አባላት የሚመረጡት ከፓርቲው ዝርዝር ውስጥ ነው፡፡
ኢብራሂም በ2003 ከኤርትራ በሱዳን በመሰደድ ወደ ኒውዝላንድ የገባ ሲሆን በኒውዝላንድ ቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የጽዳት ባለሙያ ነበር፡፡ዝቅተኛ ተከፋይ የነበረ ቢሆንም እራሱን በትምህርት በማሻሻይ ወደ ፖለቲካው ዓለም ተቀላቅሏል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *