መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፣2013-የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለ 10 ሚሊዮን ብር እድለኞቹን በዛሬው እለት እንደሚሸልም አስታወቀ

አንደኛ እጣው የወጣው በሰሜን ሸዋ ከአለም ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ በምትገኘው መራቤቴ ሲሆን እድለኞቹም ሶስት ስለመሆናቸው የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አቶ ቴድሮስ ነዋይ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

እድለኞች በዛሬው እለት በአደባባይ ገንዘባቸው የሚረከቡ ሲሆን ፤ 1ኛው 6 ሚሊዮን ብር 2ኛው 2 ሚሊዮን ብር 3ኛው ዕድለኛ 2ሚሊዮን ብሩን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡

እንዲሁም የዝዋይ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ማርታ ከበደ በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ በሶስት ትኬቶች 3,000,000 ብር እድለኛ ሆና ሽልማቷን መረከቧን ተናግረዋል፡፡

በዝዋይ ከተማ በባለፈው ዓመት በወጣው የዝሆን ሎተሪ አቶ መንግስቱ ጴጥሮስ በ1ኛ ዕጣ 7,000,000 ብር ዕድለኛ ሆኖ ሽልማቱን መውሰዱ ይታወቃል፡፡

ባለ 1.5 ሚሊዮን ብር እጣ መውጣቱን በመግለፅም አቶ ታምራት የማነ የተባሉ ግለሰብ እድለኛ ስለመሆናቸው ብስራት ሰምቷል፡፡

የ20 ሚሊዮን ብር እድለኛው ማንነት ባለመታወቁ አስተዳደሩ ዕድለኛውን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ/ብስራት ሬድዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *