መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፣2013-የኢትዮጵያ አየር-መንገድ፣የ5 ሳምንታት የበረራ ዕግድ ተጣለበት❗️

ሻንሀይ-ዴይሊ የተሰኘ የመረጃ ምንጭ፣የሀገሬውን የአየር እንቅስቃሴ ተቆጣጣሪ መ/ቤት በማጣቀስ ከዛሬ ረፋድ አንስቶ ባሰራጨው ዘገባው፣የኢትዮጵያ አየር-መንገድ የበረራ ዕገዳ እንደተጣለበት አውርቷል፡፡

የወሬ-ምንጩ እንዳለው፣በፈረንጆቹ ጥቅምት 6 እና በሳምንቱ ጥቅምት 13 ቀን 2020፤በሻንሀይ ፑንዶንግ አየር-ማረፊያ፣በጥቅሉ 15 የሚደርሱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው የመጡ መንገደኞች፣የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው መሆኑን ተከትሎ፣የቻይና የአየር እንቅስቃሴ ተቆጣጣሪ መ/ቤት፣አየር-መንገዱ ቢያንስ ለ5 ሳምንታት ወደ ከተማይቱ እንዳይበር አግዶታል፡፡

በዚሁ መሰረት፣5 ሳምንታትን ያህል የሚፀና እና ከ6 ቀናት በኋላ ተግባራዊ የሚደረግ የበረራ ክልከላ በኢትዮጵያ አየር-መንገድ ላይ እንደተጣለበት ተነግሯል፡፡

የቻይና የአየር-እንቅስቃሴ ተቆጣጣሪ መ/ቤት የኮሮና-ቫይረስን አስመልክቶ ያወጣው መመሪያ እንደሚያዘው ከሆነ፣የውጭ አየር-መንገዶች ካሳፈሯቸው መንገደኞች ውስጥ ቢያንስ በ5ቱ ላይ ቫይረሱ ቢገኝ፣አየር-መንገዶቹ ከሳምንት ላላነሰ ጊዜ የበረራ ዕግድ ይጣልባቸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም፣እንደ Aerofloat China Eastern እና Etihad ያሉ የአየር-መንገዶች በተመሳሳይ ወደ ሻንሀይ እንዳይበሩ ተከልክለው ነበር፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ብስራት ሬዲዮ ወደ ኢትዮጵያ አየር-መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ስልክ ደውሎ ባገኘው መልስ፣አየር-መንገዱ ከቻይና አቪየሽን መ/ቤት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን እና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ዝርዝር መረጃ እንደሚወጣ ተነግሮታል፡፡

በሄኖክ አለማየሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *