መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 11፣2013-በኢትዮጵያ ተጨማሪ 628 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 868 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 333 የላቦራቶሪ ምርመራ 628 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 118 ደርሷል።

በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 44 ሺህ 506 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 384 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 45 ሺህ 226 ሰዎች መካከል 303 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 416 ሺህ 829 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *