መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 11፣2013-በደቡብ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ ክልል ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባጋጠመው የትራፊክ አደጋ የአስራ አንድ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ6 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ከአደጋዎቹ መካከል የአምቡላንስ ተሸከርካሪ ከባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ በተለምዶ ባጃጅ ጋር ተጋጭቷ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በሳምንቱ ዉስጥ የሟቾች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን የሳምራዊት ስዩም ዘገባ ያስረዳል፡፡

አደጋዎቹ በሀድያ ዞን ሊሞ ፣በቤን ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ፣በከንባታ ጠንባሮ ዞን አደሮ ጮንጮ ፣ በወላይታ ዞን ሲንዶ ኮይሻ ፣፣በጋሞ ዞን ግራብ አባያ ፣ጉራጌ ዞን ቀቤና ፣በዳውሮ ዞን ሆጫ ወረዳዎች ደርሰዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ ፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት እና ጥንቃቄ ጉድለት ስለመሆኑ በደቡብ ክልል ትራፊክ አደጋ መከላከል ቁጥጥር ቢሮ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *