መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 11፣2013-የጋዜጠኛው ጀማል ካሾጊ እጮኛ በአሜሪካ ፍርድ ቤት ተገኝታ ከግድያው ጀርባ የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል እጅ አለበት ስትል ተናገረች

የሳዑዲ አረቢያን መንግስት የመብት ረገጣ አእንዲሁም በየመን እርስ በእርስ ቀውስ ያለውን ሚና በመተቸት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ እንዲገደል የሆነው በአልጋ ወራሹ ልዑል ቢን ሰልማን ትዕዛዝ ነው ስትል የካሻግጂ እጮኛ ሀቲስ ሴንጊዝ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ በትላንትናው እለት በፍርድ ቤት ቀርባ ተናግራለች፡፡

በአሜሪካ የሳዑዲ ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ ዝምታን የመረጠ ሲሆን ቢን ሳልማን እጄ የለበትም ሲሉ ያስተባብላሉ፡፡

በአሜሪካ አልጋ ወራሹ ልዑሉን የተመለከተ ክስ በፍርድ ቤት ሲመለከት ሁለተኛው ሲሆን የቀድሞ የሳዑዲ አረቢያ የደህንነት ኀላፊ ላይ በካናዳ የገዳይ ቡድን ልከዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *