መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 11 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ከጥቅምት 5 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባጋጠመው ዘጠኝ የትራፊክ አደጋ የአስራ አንድ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ1 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ከደረሱት አደጋች ውስጥ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈው በእግረኞች ላይ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

አደጋዎቹ በምስራቅ ጎጃም፣በደቡብ ወሎ፣በደቡብ ጎንደር እና በአዊ ዞን ደርሰዋል፡፡

የአደጋዎቹ መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት እና ጥንቃቄ ጉድለት ስለመሆኑ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዋና ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሳፍንት እሸቴ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *