መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-ትናንት ሌሊት ራስ ደስታ አካባቢ በአንድ የስፖንጅ መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 500ሺ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለከተማ ራስ ደስታ አካባቢ አልካን ኮሌጅ አቅራቢያ በሚገኝ የስፖንጅ መጋዘን መነሻዉ ያልታወቀ የእሳት አደጋ ጥቅምት 11 ከሌሊቱ 6፡03 ላይ አጋጥሟል፡፡

አደጋዉ የስፖንጅ መጋዘን ላይ የደረሰ ሲሆን 500ሺ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡አደጋዉን ለመቆጣጠር የድንገተኛ አደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን በአዲስ አበባ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋዉን በቁጥጥር ስር ለማዋል 62 የአደጋ ሰራተኞችና 12 የአደጋ ተሸከርካሪ ተሰማርቶ ነበር፡፡84ሺ ሊትር ዉሃና 200 ሊትር ፎም አደጋዉን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ዉሏል፡፡

አደጋዉን በቁጥጥር ስር ለማዋል 3 ሰዓት ከ37 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን በሰዉ ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አቶ ጉልላት ጌታነህ ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *