መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-ኢራንና ሩሲያ በአሜሪካ መራጮች ዙርያ መረጃ አላቸዉ ሲል ኤፍ ቢ አይ አስታወቀ

የአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት ቢሮ ባለስልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ ኢራን ለዲሞክራት መራጮች የማስፈራሪያ የኢሜል መልዕክት ልካለች ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡የብሄራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ኢራንና ሩሲያ የአንዳንድ መራጮች የምዝገባ መረጃ አላቸው ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ 13 ቀናቶች ብቻ የቀሩት ሲሆን ይህ መረጃ ይፋ መደረጉ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ምርጫዉ በዉጪ አካላት ጣልቃ ሊገባበት ይችላል የሚለዉን ስጋት መረጃዉን አጠናክሮታል፡፡፡

በ2016 ምርጫ የዲሞክራቶች የኮምፒዉተር ሲስተም በበይነ መረብ ጠላፊዎች መጠለፉ የሚታወስ ሲሆን ሁኔታዉ ያለፈዉን ክስተት የሚያስታዉስ ሆኗል፡፡ኤፍ ቢ አይ የ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ በሩሲያ መንግስት በተደገፈ የበይነ መረብ ጠላፊዎች የጥቃት ሰለባ መሆኑን ድምዳሜ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በክርምሊን የታገዙት የበይነ መረብ ጠላፊዎቹ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ገጽ ትስስር በማሰራጨትና የሳይበር ጥቃት እንደፈጸሙ በዚህ የፕሬዝዳንታዊ እጩ ተፎካካሪ የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ተጎጂ ሆነዋል፡፡

የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር ክርስቶፎር ሬይ ከብሄራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ የምርጫ ሥርዓት አሁንም አስተማማኝ እና ጠንካራ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *