መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ አስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሰሩት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ፈቅዶ የተሞከረበት ብራዚላዊ ህይወቱ ማለፉን የብራዚል የጤና ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ አስትራዜኔካ ምርምሩን እንደማያቋርጥ ይፋ አድርጓል፡፡

~ በስፔን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን መበለጡ ተሰማ፡፡በቫይረሱ ህይወታቸዉ ያጡ ሰዎች ቁጥር 34,366 ደርሷል፡፡

~ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሮበርት ኦ ብሪን ቻይና በክፍለ ዘመኑ ስጋት ደቅናለች ሲሉ ተናገሩ፡፡የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በኮሮና ቫይረስ መነሻ ዙርያ እዉነታዉን በመደበቅና በንግድ ፉክክር ዙርያ ለአሜሪካ የደቀነዉን ስጋት ኦ ብሪን አንስተዋል፡፡

~ በናይጄሪያ በአንድ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የሚዲያ ተቋም ላይ ጥቃት ተሰነዘረ፡፡በሌጎስ ኔሽን ጋዜጣ የተባለ የጥቃት ሰለባ የሆነ ሲሆን አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ መቃጠሉ አይዘነጋም፡፡የጸጥታ አካላት የሀይል እርምጃን በመቃወም የተጀመረዉ ዉጥረት አሁንም አልተረጋጋም፡፡

~ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ቡድን አምኒስቲ ኢንተርናሽናል በናይጂሪያ ተቃዉሞ 12 ሰዎች መገደላቸዉን አወገዘ፡፡በሌጎስ ከተማ የተገደሉት ተቃዋሚዎች ያልታጠቁ ነበሩ ሲል ተቋሙ አስታዉቋል፡፡

~ በጊኒ የቅድመ መራጮች ዉጤት የ82 አመቱ አዛዉንት ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ስለማሸነፋቸዉ ምንጮች መጠቆማቸዉን ተከትሎ ግጭት ተቀስቅሷል፡፡ከባድ የፍንዳታ ድምጽ እየተሰማ ሲሆን በመዲናዋ ኮናክሪ የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏል፡፡

~ አሜሪካ 1.8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለታይዋን ለማካሄድ ዉሳኔ አሳለፈች፡፡ታይዋን ግዛቴ ናት ከሌላ አካል ጋር እንዲህ ዓይነቱን ድርድር ማድረግ አትችልም የምትለዉ ቻይና በዉሳዉ ተቆጥታለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *