መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊዮን በላይ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ።

ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዶምቦስኮ ት/ቤት አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ቲም ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ይርጋ ተካ እንደገለፁት በህዝብ ጥቆማ የተያዘው 2 ሚሊዮን 222 ሺህ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር የዋለው የብሄራዊ ባንክ መመሪያን በመተላለፍ በግለሰብ እጅ መገኘት ከሚፈቀደው በላይ ሆኖ በመገኘቱ ነው።

የባንክ አዋጅ 591/2008 እንደሚያስረዳው በአንድ ግለሰብ እጅ መገኘት ያለበት የብር መጠን 1.5 ሚሊዮን እና ከዚያ በታች ሲሆን ይህንን ተላልፎ ከተጠቀሰው የብር መጠን በላይ ይዞ የተገኘ ግለሰብ ገንዘቡ እንደሚወረስ በግልጽ ተቀምጧል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *