መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 12፣2013-በሐዋሳ ከተማ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የኮማንዶ ትርኢት እየተካሔደ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸው የኮማንዶ አባላት የልዩ ግዳጅ ትርኢት እያሳዩ ነው።

በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፓሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የአየር ወለድ አባላት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ ከሔሊኮፒተር የፎቅ ዝላይ በማድረግ የጸረ ሽብርና ጥቃት ትዕይንት አሳይተዋል።

በቶጋ፤ በወንዶ ጢቃና በወንዶ ገነት አካባቢ የሜዳና የገደል ዝላይ፤ ከሒሊኮፒተር በፓራሹት በመውረድ ትዕይንቱን እያሳዩ ነው።

የልዩ ሀይል ፀረ ሽብር ስልታዊ ተኩስ ትርኢትም በዝግጅቱ እየታየ ይገኛል።

በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ሀይል የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት የባህር ላይ ትርኢት በልዩ ሁኔታ እያቀረቡ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማዘዣ በአምስት ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ አባላት ነገ እንደሚያስመርቅ ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *