መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 18፤2013-ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት መገደላቸው ተሰማ

መስሪያ ቤቱ ያወጣው የሃዘን መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል

“የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የስራ ባልደረቦች የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በዚህም የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራሮች እና ሰራተኞች ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡” ሲል ትምህርት ሚኒስቴር መልዕክቱን በይፋዊ ገፁ አጋርቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *