መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 20፣2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች

~ በታንዛኒያ ባሳለፍነው እሮብ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት እንደማይቀበል የሀገሪቱ ዋንኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አስታወቀ።ምርጫው ፍትሃዊ አልነበረም ሲሉ የተቃዋሚው ፓርቲ ፕሬዝዳንት ቱንዱ ሊሱ ተናግረዋል።

~ አሜሪካ በታንዛኒያ የተካሄደው ምርጫ ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ እንዳላት አስታወቀች።ባሳለፍነው እሮብ በተካሄደው ምርጫ የፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ አስተዳደር 85 በመቶ የመራጮችን ድምፅ አግኝቷል ተብሏል።

~ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለእስልምና ጥላቻ አራምደዋል በሚል ተቃወሙ።

~ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 18 ሰዎች ተገደሉ።በሰሜን ምስራቃዊ ኪቩ ግዛት ለደረሰው ጥቃት የአላይድ ዲሞክራቲክ ሀይሎች ሀላፊነቱን ወስዷል።

~ አሜሪካ ወደ የመን ሲጓጓዙ የነበሩ 11 ሚሳኤሎችን በቁጥጥር ስር አዋለች።በተመሳሳይ 11 ኩባንያዎች ከኢራን ጋር ይሰራሉ በሚል በዋሽንግተን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

~ የእስራኤል ፍርድ ቤት ፍልስጤማዊው የ13 ዓመት ታዳጊ ጥቃት ሊፈፅም ነበር በሚል በሶስት ዓመት እስር እንዲቀጣ መወሰኑ ቅሬታ አስነሳ።

~ በቬትናም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *