መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2013-በአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት የነገውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሶማሊያ ህዝቦች በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት መሆኑ ተሰማ

የ 15ሚሊየን ህዝቦች መኖሪያ በሆነችው ሶማሊያ የአሜሪካ ፖሊስ በሀገሪቱ ላይ በተዘዋዋሪ ሆነ በቀጥታ ተፅዕኖ ያሣድራል፡፡

ሶማሊያ ነፃነቷን ካገኘች ከ 1960 አንስቶ የአሜሪካ መሪዎች እና ሶማሊያ የተለያዩ ግንኙነት ውስጥ መግባታቸውን የአለም አቀፍ ግንኙነት ጥናት መምህር የሆኑት የሶማሊያ ብሄራዊ ዩኒቨርሲቲ ሀሰን ሼኪ አሊ ተናግረዋል፡፡

ዋንኛ ምክንያት ደግሞ ሶማሊያ የጆኦግራፊ አቀማመጥ ነው ብለዋል፡፡ ሶማሊያ በምስራቃዊ ከህንድ ውቅያኖስ ፣ በሰሜን ከኤደን ባህረሰላጤ የምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ ሃገር ነች፡፡

30ሺ ያህል መርከቦች ነዳጅን ጨምሮ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ቁልፍ የትራንዚት መዳረሻ ነው፡፡

በህንድ ውቅያኖስ እና ሜዲትራኒያን ባህር መካከል እንደመገኘቷ ወሳኝ ናት፡፡ ሀሰን አሜሪካ በሶማሊያ ያላት የራሷን ፍላጎት ለማሳካት ትሰራለች ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *