መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በኮሎምቢያ የቀድሞ አማፂ ቡድን ፋርክ አባላት በመዲናዋ ቦጎታ ግድያ እንዲያበቃ ጥሪ አቀረቡ፡፡ በ2016 የፋርክ አማፂ ቡድን አባላት በሰላም ስምምነት ከኮሎማቢያ መንግስት ቢደርሱም ከዚያ ጊዜ አንስቶ 236 አባላቶች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

~ በፊሊፒንስ ባጋጠመው ከባድ ወጀብ እና አውሎንፋስ ቢያንስ 10 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 3ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከ 300 በላይ ቤቶች ወድመዋል፡፡

~ የእስራኤል አረብ ሀገራትን የሚተቹ የትዊተር ገፆች መዘጋጀታቸው ተሰማ፡፡ የተዘጉት የቲውተር ገፆች በእስራኤል ጥያቄ ሲሆን ባለቤትነታቸው የፍልስጤም እንደሆነ ታውቋል፡፡ እስራኤል 128 የቲውተር አካውንቶች እንዲዘጉለት ጠይቆ ነበር፡፡

~ የህንድ ወታደሮች በካሽሚር ከፍተኛ የተባለው አማፂ ቡድን መሪን መግደላቸው ተሰማ፡፡ ኮማንደሩ የሂዝቦላ ሙጃሂዲን አማፂ ቡድን መሪ ሳፋሁላ ሚራ ይባላል፡፡ ህንድ በምታስተዳድራት የካሽሚር ግዛት መገደሉ ተረጋግጧል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *