መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 25፣2013-“በተልዕኮ ላይ የነበረዉ የመከላከያ ሰራዊት በከሀዲ ቡድን ጥቃት ተፈፅሞበታል❗️”የኢ.ፌ.ድ.ሪ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከደቂቃዎች በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል
” በመከላከያ ሰራዊት ላይ ከባድ ወረራ እና የክህደት ተግባር ተፈፅሞበታል ” ሲሉ ተናግረዋል::
አያይዘዉም ” በትግራይ የመሸገዉ ህገ-ወጥ ቡድን በልዩ-ሀይሉ አማካኝነት በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ለመፈፀም አሁንም እየተንቀሳቀሰ ነዉ ” ብለዋል::
የሆነዉ ሆኖ ሰራዊቱ የተፈፀመበትን ጥቃት መክቶ የተሰጠዉን ተልዕኮ በመወጣት ላይ ነዉ ሲሉ ም/ጠ/ሚሩ ንግግራቸዉን ደምድመዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *