መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 26፣2013-በነባራዊ ሁኔታ ምክንያት የደም እጥረት አለመከሰቱን የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ

ብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ደም ወደ ጎንደር በመላኩ ደም በባንኩ ውስጥ የለም እየተባለ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በአገልግሎቱ የደም ለጋሾች ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተመስገን አበጀ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናገረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቂ የሚባል ደም በባንኩ ውስጥ ባይኖርም እጥረት አለ ማለት ግን አይቻልም ሆኖም እጥረቱ ሊከሰት የቻለው ግን ትምህርት ቤቶች እንዲሁም አንዳንድ ተቋማት ዝግ ሆነው በመቆየታቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ዳይሬክተሩም ጨምረው ከክልል ከተሞች የደም ይቅረብልን ጥያቄ አለመቅቡን አስረድተዋል።

በጎንደር ከተማ አራት ዞኖች እና ሪፈራል ሆስፒታሎች በመኖራቸው በደም እጥረት የሚሞቱ እናቶች እንዳይኖሩ እንዲሁም በሀገሪቷ ባለው አለመረጋጋት አማካኝነት ችግር ቢከሰት ደም እጥረት እንዳይኖር ደም ልገሳ ፕሮግራም በማዘጋጅት ላይ መሆናቸው የጎንደር ከተማ መስተዳዳር የኮሚኒኬሽን ሃለፊ አቶ ቻላቸው ዳኘው በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ጎንደር አሁን ወደ ቀደሞ እንቅስቃሴዋ መመለሷ ያስረዱት ሃላፊው ወጣቱ አካባቢውን እና በከተማዋ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማትን ተደራጅቶ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *