መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 28፤2013-አንዳንድ መረጃዎች ስለ 46ኛው የአሜሪካፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

እ.ኤ.አ በ1972 ባይደን የመጀመሪያ ባለቤታቸውን ኒሊያ እና ሴት ልጃቸውን ናሆሚ በመኪና አደጋ የተነጠቁ ሲሆን በ2015 ሌላኛውን ወንድ ልጃቸው በጭንቅላት ካንሰር ተነጥቀዋል።

ባይደን ከመጀመሪያ ፍቅረኛቸው ጋር በነበራቸው ሁለተኛው የእራት ግብዣ ቀጠሮ ላይ በኪሳቸው በቂ ገንዘብ አልነበረም።

46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ጆ ባይደን ወደ ቬትናም ጦርነት ሊያመሩ የነበረ ቢሆንም የአስም ህመም ስለነበረባቸው ከጦርነቱ ቀርተዋል።

የቀድሞ መምህሯ የጆ ባይደን ሁለተኛ ባለቤት ጂል ትሬሲ ጃኮቦ ቀጣይ ቀዳማዊት እመቤት ትሆናለች።

እ.ኤ.አ በ1988 እና በ2008 ባይደን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው ነበር።በአሜሪካ ታሪክ በእድሜ ትልቁ ፕሬዝዳንት በመሆን ነጩ ቤተመንግስት ገብተዋል።

ሲጋራ አጭሰውም ሆነ አልኮል ጠጥተው የማያውቁት ባይደን ምክንያታቸው ደግሞ ቤተሰባቸው በአልኮል ሱስ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል

ባይደን የኦባማ ምክትል በነበሩበት ዘመን የአሜሪካን የኢራቅ ፖሊሲ ቁልፍ ሚና የነበራቸው አመራር ነበሩ።

ጆ እና ጂል ባይደን የተሰኘ የረድኤት ድጋፍ የሚያደርግ ፋውንዴሽን ያላቸው ሲሆን በህፃናት፣ሴቶችና ካንሰር ላይ ትኩረቱን በማድረግ በ2007 ተመስርቷል።

በከባድ የአንገት ህመም የተነሳ ባይደን ለሁለት ጊዜ ያህል የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ህክምናን አድርገዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *