መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 28፤2013-አንዳንድ ነጥቦች በአሜሪካ ምርጫ ዙሪያ

~ አሜሪካውያን ከ20 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊውን ለማወቅ ቀናቶችን በትዕግስት እንዲጠብቁ የዘንድሮ ምርጫ አስገድዷል።

~ የአላስካ፣የፔንስልቫኒያ፣የጆርጂያና ኔቫዳ ግዛቶች የመራጮች ድምፅ እየተቆጠረ ሲሆን እስካሁን ድረስ አሸናፊው አልተለየም።

~ በአሪዞና ግዛት ባይደን እንዳሸነፉ መረጃዎች ቢጠቁሙም የምርጫ የስራ ሀላፊዎች ግን አሁንም በፖስታ የተላኩ ድምፆች እየተቆጠሩ ነው ብለዋል።

~ የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ በቀጣዩ ምርጫ ያሸነፈው ፕሬዝዳንት በኢራን የኒውክሌር መርሃግብር ዙርያ የተደረሰበትን የ2015ቱን ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

~ የድምፅ ቆጠራ በሚደረግባቸው የምርጫ ማዕከላት አካባቢ ሽጉጥ የታጠቁ ግለሰቦች በርከት ብለው መታየታቸው ስጋት ፈጥሯል።

~ ትራምፕ ማስረጃ ማቅረብ ቢሳናቸውም አሁንም የድምፅ ቆጠራው እንደተጭበረበረ በመናገር ላይ ሲሆኑ በጆርጂያና ፔንስልቫኒያ እየመሩ የሚገኙት ባይደን ውጤቱን በትግስት ደጋፊዎቻቸው እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *