መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2013-በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የተጠቂዎች ቁጥር ከ 50 ሚሊዮን መብለጡ ተሰማ


የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ከ 1-25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስታውቋል፡፡
በአውሮፓ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ 12.5ሚሊዮን ሲያልፍ 305ሺህ ሰዎች ህይወታቸው ማለፏ ተረጋግጧል፡፡
በአሜሪካ ከ 10ሚሊዮን ያላነሱ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ሲረጋገጥ ከ125ሺ በላይ ሰዎች ባለፉት ሶስት ቀናት በአማካይ በየእለቱ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተረጋግጧል፡፡
ቫይረሱ በድጋሚ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰባት በምትገኘው ፈረንሳይ ባለፉት 24ሰዓት የ271 ሰዎች ሕወት አልፏል፡፡
ፖርቹጋል የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በዛሬው እለት ከቤት ያለመውጣት እቀባን ታደርጋለች፡፡
በህንድ እና ብራዚል የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር አሁንም እየጨመረ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *