መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2013-በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ጆ ባይደን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል ቀዳሚ ተግባራቸው መሆኑ ተነገረ

የባይደን የሽግግር መንግስት እቅድ በአሜሪካ ዜጎች አፍና አፍንጫቸውን እንዲሸፍኑ እና የቫይረሱን ስርጭት በሚገባ እንዲከላከሉ የሚያስችል ስራን እንደሚሰሩ ተጠቁሟል፡፡

የባይደን ትኩረት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሲስተማርክ የሚባለውን ዘረኝነት ለመቆጣጠርና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

በወርሃ ጥር ባይደን ስልጣን ሲረከቡ በድጋሚ ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አሜሪካን ለመመለስ እንዲሁም ከአለም የጤና ድርጅት አሜሪካ ለመውጣት ያሣለፈችውን ውሳኔ ይከልሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሰባት የሙስሊም ሀገራት ዜጎች እንዳይመጡ የተጣለውን ማዕቀብ እንደሚያነሱ ይጠበቃል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ ጆ ባይደን ማሸነፋቸውን ተከትሎ አሜሪካን ለመፈወስ አሁን ሰዓቱ ነው ብለዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *