መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2013-አዘርባጃን ከአርሜንያ ጋር የገባችበትን ጦርነት ተከትሎ ቁልፍ የተባለች ከተማን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተሰማ


በናጎርኖ ካራባክ የይገባኛል ግጭት የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት አሊየቪ ሹሻ በአርመኖቹ አጠራር ሹሺ የተባለችውን ከተማ በቁጥጥር ስር የሀገሪቱ ጦር ማዋሉን አስታውቀዋል፡፡
አርሜንያ በበኩሏ ጦርነቱ ቀጥሏል የተነጠቁት ከተማ የለም ስትል አስተባብላለች፡፡
የስትራቴጂ ጠቀሜታ አላት የተባለችውን ከተማ በቁጥጥር ስር የአዘርባጃን ጦር ማዋሉ ከፍተኛ ስኬት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የናጎርኖ ካራባክ ግዛት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለአዘርባጃን እውቅና የሰጠው አካባቢ ቢሆንም በአርሜንያ መንግስት የሚደገፉ የአርመን ጎሳ አባላት በስፋት ይኖሩበታል፡፡
ሀገራቱ እ.ኤ.አ በ 1994 በዚህችው ግዛት ከፍተኛ ውጊያ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *