መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 30፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ ዜናዎች

ባሳለፍነው የእረፍት ቀናቶች ከ 1600 በላይ የአፍሪካ ስደተኞች በስፔን ካናሪ ደሴቶች መግባታቸው ተሰማ፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ 20 በሚሆኑ ጀልባዎች ከ 1000 ስደተኞች ካናሪ ደሴት ደርሰዋል፡፡ ከሰሜን አፍሪካ ጠረፍ በ 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የካናሪ ደሴቶች ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞች መዳረሻ ሁኗል፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈረንሳይ ከሙስሊም የዓለም ሀገራት ጋር የገባችበትን ውጥረት ለማብረድ ወደ ካይሮ ገብተዋል፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሊድሪአን ከፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አልሲስ እና ከግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሹክሪ ጋር መክረዋል፡፡

የቱርክ የፋይናንስ ሚኒስትር ቢራት አልባያራክ ከስልጣን መልቀቃቸውን በግል የኢንስታግራም ገፃቸው አስታወቁ፡፡ በጤና እክል ምክንያት ስጣናቸው መልቀቃቸውን ያስታወቁት አልባያራክ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ሴት ልጅ ባለቤት ነው፡፡

በካሽሚር በተፈጠረ ግጭት አራት የህንድ ወታደሮች ሲገደሉ 3አማፂያን ቆስለዋል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በህንድ እና የፓኪስታን ካሽሚር በሚለየው የድንበር አካባቢ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ህንድ በጥቃቱ ዙሪያ ፓኪስታን ያሰለጠነቻቸውን ታጣቂዎች ናቸው ብትልም ፓኪስታን እጄ የለበትም ስትል ተናግራለች፡፡

የእስራኤል ካቢኔ በፍልስጤምና የጋዛ ሰርጥ አካባቢ ነዋሪዎችን ለማስፈር ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በውሳኔው መሰረት 500 ቤተሰቦች የሚሰፍሩ ሲሆን የመሰረተ ልማት ግንባታው በ 296ሺህ ዶላር ይገነባል፡፡

በማይናማር በትላንትናው እለት የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የምርጫው ውጤት በዛሬው እለት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የወቅቱ የሀገሪቱ መሪ ሱኪ ፓርቲ በምርጫው እንደሚያሸንፍ ሰፊ ግምት አግኝቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *