መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 1፤2013-በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ስድስት ናይጄሪያውያን ለቦኮሀራም ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር በሚል በቁጥጥር ስር ውለዋል

ስድስቱ ናይጄሪያውያን ግለሰቦች መቀመጫቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት በማድረግ በ2015 እና በ2016 ለቡድኑ ገንዘብ ማስተላለፋቸው ተረጋግጧል።ስድስቱ ግለሰቦች ለቡድኑ 782ሺ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ማስተላለፋቸው ማረጋገጫ ተገኝቷል።

ገንዘቡን ያስተላለፉት ግለሰቦች በናይጄሪያ የገንዘብ ምንዛሪ በህጋዊ መንገድ የሚሰሩ የቤተሰብ አባላት እንዳላቸው ተነግሯል።እነርሱን በመጠቀም ገንዘቡ ለቡድኑ እንዲደርስ ሆኗል።

ቦኮሀራም በሰሜን ምስራቃዊ ናይጄሪያ መጠነ ሰፊ የሽብር ጥቃት በመክፈት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ምክንያት የሆነ ቡድን ነው።የቡድኑ መሪ አቡበከር ሼካው አሁንም በቁጥጥር ስር አልዋለም።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *