መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 3፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

🇨🇮በአይቮሪኮስት የሚገኙ የፖለቲካ ተቀናቃኞች በሀገሪቱ ሰላም እንዲመጣ ከዉሳኔ ላይ ደረሱ፡፡በሀገሪቱ በተካሄደዉ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኦታሬ በድጋሚ ማሸነፋቸዉ ባስከተለዉ ዉዝግብ 85 ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን የሀገሪቱ መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡

🇭🇰ከሆንግ ኮንግ ምክር ቤት ተቃዋሚዎች ከምክር ቤቱ መልቀቃቸዉን ቻይና አወዘገች፡፡በቻይና የተረቀቀዉን የብሄራዊ ደህንነት ህግ በመቃወም 4 አባላት በምክር ቤቱ መታገዳቸዉን ተከትሎ ሌሎች 15 ሀገሮቻቸዉ ከምክር ቤቱ ራሳቸዉን አግለዋል፡፡

🇺🇸ኒዉዮርክ የሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለማስቀረት የመጨረሻ እድል ያለችዉን እንቅስቃሴ የሚከለክል ህግን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች፡፡ህዝባዊ ቦታዎች ላይ ሰዎች ከ10 በላይ ሆነዉ መሰብሰብ የማይችሉ ሲሆን በሰዓት እንዲገደቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

🇺🇸ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሮን ካሌን የዋይት ሀዉስ ዋና የስራ ሀላፊ አድርገዉ እንደሚሾሙ አስታወቁ፡፡እ.ኤ.አ ከ1980 አንስቶ የባይደን የቅርብ የስራ አጋር በመሆን ሰርተዋል፡፡

🇵🇸በእስራኤል ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ የሚገኙ 123 ፍልስጤማዉያን ታራሚዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተሰማ፡፡በ17 የእስራኤል ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ከ7ሺ በላይ የፍልስጤም ታራሚዎች እንደሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አስታዉቀዋል፡፡

🇲🇽በሜክሲኮ ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የ588 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡በአጠቃላይ በቫይረሱ በሜክሲኮ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 986,177 ሲደርስ የ96,430 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

🇦🇲የአርሜንያ ጠቅላይ ሚንስትር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚደረግባቸዉን ግፊት ተቃወሙ፡፡ጠ/ሚ ኒኮላ ፓሺያን የተኩስ አቁም ስምምነት ከአዘርባጃን መንግስት ጋር መድረሳቸዉ እንዲሁም በዉጊያዉ አዘርባጃን በሀይል የተቆጣጠረችዉ ስፍራ ላይ እንድትቆይ ሩሲያ ባሸማገለችዉ ጥሪ መስማማታቸዉ ተቃዋሚዎችቸዉን አስቆጥቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *