መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 3፤2013-የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦
ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
አቶ አባይ ፀሃዬ
ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
አቶ ጌታቸው ረዳ
አቶ አፅበሃ አረጋዊ
አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *