መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 4፤2013-በአሜሪካ የምርጫ ደህንነት ባለስልጣናት የትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል ውንጀላ ውድቅ አደረገ


የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል የምርጫ ባለስልጣናት እንደተናገሩት የ2020 የአሜሪካ ምርጫ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ ነበረ ሲሉ የትራምፕ ክስ አጣጥለዋል፡፡
ትራምፕ ያለ በቂ ማስረገጫ እኔን የመረጡ 2.7 ሚሊየን መራጮች ድምጽ እንዲጠፋ ተደርጓል ሲሉ ከሰዋል፡፡የዲሞክራቱን ጆ ባይደን አሸናፊነት ትራምፕ አሁንም አልተቀበሉም፡፡
ውጤቱ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ይፋ የተደረገ ቢሆንም የተወሰኑ ቆጠራዎች ግን አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው ፡፡
ትራምፕ በቁልፍ ግዛቶች ውጤቶች ላይ በርካታ የሕግ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በምርጫ ማጭበርበር ያልተረጋገጡ ክሶችን ይፋ አድርገዋል ፡፡
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እየቀረበ ያለዉ ክስ ዴሞክራሲን የሚያናጋ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *