መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፤2013-የእንግሊዝ ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ የስራ አጋራቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ራሳቸውን ማግለላቸው ተሰማ

በእንግሊዝ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል ከሆነው አንደርሰን ጋር ባሳለፍነው ሃሙስ ለ35ደቂቃ ቦሪስ ጆንሰን ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡

አንደርሰን በተደረገላቸው ምርመራ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ ቦሪስ ጆንሰን ራሳቸውን አግልለዋል፡፡

በቲውተር ገፃቸው ላይ ከእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት (NHS) ራሴ እንዳገልና እንድመረመር መመሪያ ተሰጥቶኛል ያሉት ቦሪስ ጆንሰን የቫይረሱ ምንም ምልክት የለብኝም ብለዋል፡፡

የ56ዓመቱ ቦሪስ ጆንሰን በወርሃ መጋቢት በቫይረሱ ተጠቅተው የነበረ ሲሆን በፅኑ ህሙማን መከታተያ ገብተው ማገገማቸው ይታወሳል፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት ከእንግሊዝ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አስገዳጅ ህግ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *