መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፤2013-የፔሩ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሚሪኖ በተነሳባቸው ከባድ ተቃውሞ ከስልጣን መልቀቃቸው ተሰማ

የፔሩ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በመሆን ከቀናት በፊት የተሾሙት ማኑኤል ሚሪኖ አንድ ሳምንት እንኳን በስልጣን ላይ ሳይቆዩ ተወግደዋል፡፡

በሀገሪቱ በተፈጠረ ከባድ ተቃውሞ ሁለት ወጣቶች መገደላቸው እንዲሁም በርካቶች የጉዳት ሰለባ በመሆናቸው የዜጎች ቁጣ
ተቀስቅሷል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ ሚሪኖ በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ትናንትና ምሽት ለሰላም እና አንድነት ጥሪ በማድረግ ስልጣን ለቀዋል፡፡

የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማርቲን ቪዝካራ በምዝበራ ቅሌት ተከሰው ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ኮንግረሱ ባሳለፍነው ማክሰኞ ማሪኖ ሾሟል፡፡

የማሪኖ ሹመት በመመቃወም በህዝብ እንደራሴዎቹ ም/ቤት መፈንቅለ መንግስት ተከሂዷል ያሉ ዜጎች ስልጣን እንዲለቁ አድርገዋል።

በስምኦብ ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *