መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2013-በአፍሪካ የነጻ ገበያ ቀጠና በቀጣዩ ጥር ወር እንደሚጀምር ይፋ ተደረገ

የፓን አፍሪካ የነጻ ንግድ ገበያ በወርሃ ሀምሌ ለማስጀመር እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ይህንን ማሳካት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

የአፍሪካ አህጉር የነጻ ንግድ ቀጠና ዋንኛ ዓላማ የአፍሪካን ህዝቦች ኑሮ በማሻሻል ያሉትን ተግዳሮቶችን በመቀነስ ያለዉን ምቹ እድል ለመጠቀም ያስችላል በሚል ታምኖበታል፡፡

ከ1ቢሊየን በላይ የአፍሪካን ህዝብ በነጻ ንግድ በማስተሳሰር እስከ 3 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዝዉዉር በዓመት እንዲኖር ያስችላል፡፡ከታሪፍ እና ከሌሎች አሰራሮች ጋር ተያይዞ የነበረዉ ምክክር በተያዘዉ ሳምንት በድጋሚ ይመለሳል፡፡

ከወርሃ ጥር አንስቶ የንግድ እንቅስቃሴዉ እንዲመለሰ ከ54ቱ የአህጉሩ ሀገራት 30 ያህሉ አዉንታዊ ምላሽ በስምምነቱ ላይ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በአፍሪካ የአኮኖሚ ቁንጮ በሆነችዉ ናይጄሪያ ከህገወጥ የንግድ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ አሁንም ድንበሮቿ ዝግ እንደሆኑ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *