መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2013-ኢትዮጵያ 13 ቢሊዮን ብር የተላላፊ በሽታን ለማስቀረት በሚል በየዓመቱ ወጪ ታደርጋለች ተባለ

25በመቶ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ ከሚመዘገበው ሞት በተላላፊ በሽታ የሚከሰት ስለመሆኑ በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በጥቅሉ 30 በመቶ በኢትዮጵያ የሚመዘገው ሞት በተላላፊ በሽታ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ 13ቢሊዮን ብር የተላላፊ በሽታን ለማስቀረት በሚል በየዓመቱ እያጣች ትገኛለች

በኢትዮጵያ ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች በአንደኛ ደረጃ ኒሞኒያ ፣ ሁለተኛ ተቅማጥና ትውከት እንደሆም ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል።

ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለማስቀረት የንፁህ መጠጥ አቅርቦትና የመፀዳጃ ቤት በአግባቡ መገንባት እንደሚያስፈልግ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ትዕግሥት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *